ወደ ኖቭልዋን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ገጽ
ወደ ኖቭልዋን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ገጽ
ኖቭልዋን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
(Novel One Trading PLC)
ኖቭልዋን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በኢትዮጵያ የ Taihao ጎማዎች ብቸኛ አስመጪ ድርጅት ነው። ለግንባታ፣ ለማዕድን እና ለከባድ የትራንስፖርት ዘርፎች የሚሆኑ ጥራት ያላቸው፣ በልዩ ቴክኖሎጂ (Anti-Abrasive) የተሰሩ የሎደር እና የከባድ ማሽኖች ጎማዎችን በሀገር ውስጥ እናቀርባለን።
ድርጅታችን የደንበኞችን የስራ ጊዜ እና ወጪ በማስላት፣ ረጅም አገልግሎት የሚሰጡ እና ዘላቂነት ያላቸው ምርቶችን በማቅረብ የታወቀ ነው። የኖቭልዋን ትሬዲንግ ዋና ዓላማ የኢንዱስትሪውን ውጤታማነት በከፍተኛ ደረጃ የሚያግዙ፣ ተወዳዳሪ ዋጋ ያላቸውን እና ለከባድ ጫና የተዘጋጁ ጎማዎችን አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለደንበኞቻችን ማዳረስ ነው።
ኩባንያችን ለደንበኞች የሚያቀርባቸው የ Taihao ጎማዎች በከፍተኛ ጫና ውስጥም እንኳ ቅርጻቸውን የማይቀይሩ፣ በቀላሉ የማይላላጡ እና ለአንድ ሰዓት ሥራ የሚወጣውን ወጪ (Cost per Hour) የሚቀንሱ ናቸው። ኖቭልዋን ትሬዲንግ ጥራትን፣ ታማኝነትን እና ሙያዊ ድጋፍን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያን የግንባታና የትራንስፖርት ዘርፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ይሰራል።