የግብርና ጎማዎች
Agricultural Tyre
Agricultural Tyre
የእርሻ መሣሪያዎች (Agricultural machines) በዘመናዊ ግብርና ውስጥ ምርታማነትን ለመጨመር፣ የጉልበት ሥራን ለመቀነስ እና ሥራን በፍጥነት ለማከናወን የሚረዱ መሣሪያዎች ናቸው።
ምርታማነትን መጨመር፦ በሰው ኃይልና በከብት ከሚታረሰው በላይ ሰፊ መሬትን በአጭር ጊዜ በማረስ ምርትን ያሳድጋሉ።
ጊዜና ጉልበት መቆጠብ፦ ለቀናት የሚፈጅን ሥራ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በማጠናቀቅ የገበሬውን ድካም ይቀንሳሉ።
ጥራትን መጠበቅ፦ ዘርን በእኩል ርቀት ለመዝራትና ምርትን ሳይባክን ለመሰብሰብ ይረዳሉ።
ወጪን መቀነስ፦ ምንም እንኳን የመግዣ ዋጋቸው ቢወደድም፣ በረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ የሠራተኛ ወጪን ይቀንሳሉ
ለግብርና ስራዎች የሚሆኑ የጎማ አይነቶች
ጥቅማቸው፦ ለስላሳና እርጥብ በሆኑ የእርሻ መሬቶች ላይ ማሽኑ ሳይሰምጥና መሬቱን ሳያበላሽ እንዲንቀሳቀስ ይረዳሉ፡፡
የሚገጠሙባቸው ማሽኖች፦ ትራክተሮች፣ ምርት ሰብሳቢ ማሽኖች (Harvesters) እና የመስኖ ማሽኖች ላይ ይገጠማሉ፡፡
የፓተርን ልዩነት፦ እንደ R-1 (ለመደበኛ እርሻ) እና R-2 (ለረግረግ ወይም ለሩዝ እርሻ) ያሉ ፓተርኖች አሏቸው፡፡ የፓተርን ጥርሶቻቸው እርስ በርስ የራቁ ናቸው፤ ይህም በጥርሶቹ መካከል የሚገባው ጭቃ በቀላሉ ራሱን እንዲያጸዳ (Self-cleaning) ለማድረግ ነው፡፡
MR-1 የግብርና ጎማዎች በዋነኝነት በትራክተር የፊት ጎማነት (Tractor Front Tires) የሚያገለግሉ ሲሆን፣ የጎማው ላይኛው ክፍል ብዙ መስመሮች ያሉት ዲዛይን (Multi-Rib) አላቸው።
አገልግሎት፦ በእርሻ ማሳዎች ውስጥ ለሚከናወኑ የተለያዩ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች እና ለአጭር ርቀት የትራንስፖርት አገልግሎት ለሚውሉ ትራክተሮች።
ጥቅማቸው እና ባህሪያቸው፦
ቀላል መሪነት (Excellent Steering)፦ ማሽኑ በቀላሉ አቅጣጫውን እንዲቆጣጠር እና ጥግ እንዲይዝ ይረዳል።
አፈርን አለመጨፍለቅ፦ አፈሩን እምብዛም ሳይጫን በማለፍ የተክሎችን ሥር እንዳይጎዱ ያደርጋል።
ጥንካሬ፦ ሰፊ የመርገጫ ገጽ (Wide driving surface) ስላለው ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚሆን የክብደት መሸከም አቅም አለው።
R-1 የግብርና ጎማዎች በዓለም ዙሪያ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን፣ መካከለኛ ጥልቀት ያላቸው የጎማ ጥርሶች (Moderate Bar-Lugs) ያሏቸው ሁለገብ ጎማዎች ናቸው።
አገልግሎት፦ ማረስ፣ መዝራት፣ ማዳበሪያ መበተን እና ምርት ማጓጓዝን ጨላለ ለተለያዩ አጠቃላይ የእርሻ ሥራዎች።
ጥቅማቸው እና ባህሪያቸው፦
ሚዛናዊ የመሳብ ኃይል (Good Traction)፦ በደረቅ እና መካከለኛ እርጥበት ባላቸው የእርሻ መሬቶች ላይ በጥሩ ሁኔታ ይንቀሳቀሳል።
ራሱን የማጽዳት አቅም (Self-Cleaning)፦ ጥርሶቹ አፈርንና ጭቃን በቀላሉ አራግፈው እንዲወጡ ተደርገው በመሠራታቸው፣ የጎማው የመያዝ አቅም አይቀንስም።
ዘላቂነት፦ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የጎማ ውህድ (Anti-Abrasive Compound) የተገጠመለት በመሆኑ የእርሻ ሥራን ከጎዳና ጉዞ ጋር አስተባብሮ ለመጠቀም ይመረጣል።
R-2 የግብርና ጎማዎች እጅግ በጣም እርጥበት አዘል በሆኑ እና ጭቃማ ማሳዎች ውስጥ የሚያገለግሉ ልዩ ጎማዎች ናቸው። ጥርሶቻቸው ከመደበኛው የ R-1 ጎማ በሁለት እጥፍ ያህል ጥልቅ ናቸው።
አገልግሎት፦ በውሃ በተጥለቀለቁ ማሳዎች (እንደ ሩዝ ማሳ) እና በከባድ ጭቃማ ቦታዎች ውስጥ ለሚሠሩ ማሽኖች።
ጥቅማቸው እና ባህሪያቸው፦
ከፍተኛ የጭቃ መያዝ አቅም፦ እጅግ ጥልቅ የሆኑት የጎማ ጥርሶች በጭቃ ውስጥ በጥልቀት በመግባት ማሽኑ እንዳይንሸራተት እና እንዳይቆም ያደርጉታል።
የማያቋርጥ እንቅስቃሴ፦ በውሃ በተሞሉ ወይም ዝናብ በነካቸው ለስላሳ መሬቶች ላይ ሳይሰምጡ በብቃት እንዲንቀሳቀሱ ያስችላል።
ጠንካራ አካል፦ ጎማው በከባድ ጫና ውስጥ ቅርጹን እንዳይቀይርና ጥንካሬውን እንዲጠብቅ ተደርጎ የተሠራ ነው።
ሌሎች የግብርና ጎማዎች(pattern) አይነት (size) ቁጥር ለማግኘት እዚህ ይጫኑ drive.google.com/file/d/1vbMqbkNXxY8kRiAeh4EhhnNTxZM1zLMC/view?usp=sharing
🔻