ጥያቄ፦ "ጎማው በድንጋያማ ቦታ ላይ ቶሎ አይላላጥም/አይቆራረጥም?
ሳይንሳዊ ምላሽ፦ "ታይሃኦ ጎማዎች የተሰሩት Anti-Abrasive ከተባለ ልዩ የጎማ ውህደት ነው። ይህ ውህደት በጎማው ሞለኪውሎች መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር፣ ጎማው ከድንጋይ ጋር በሚፈትግበት ጊዜ የሚፈጠረውን ግጭት (Friction) እና ሙቀት ይቋቋማል። ይህም ጥርሶቹ ሳይቆራረጡ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ ያደርጋል።
ጥያቄ፦ "የታይሃኦ ጎማዎች ዋጋ ከሌሎች የቻይና ጎማዎች ለምን ይለያል?"
ሳይንሳዊ ምላሽ፦ "የጎማ ዋጋ መለካት ያለበት በግዢ ወቅት ባለው ዋጋ ሳይሆን፣ ጎማው በሚሰጠው የአገልግሎት ሰዓት (Cost per Hour) ነው። የታይሃኦ ጎማዎች በልዩ Anti-Abrasive Compound ስለሚሰሩ፣ ከመደበኛ ጎማዎች ከ 20% እስከ 30% ተጨማሪ የሥራ ሰዓት ይሰጣሉ። ይህም ማለት ምንም እንኳ የግዢ ዋጋው ጥቂት ቢጨምርም፣ በአንድ ሰዓት ሥራ ላይ የሚወጣው ወጪ ግን ከሌሎች ያነሰ ነው።"
ጥያቄ፦ "የጎማው ጥንካሬ (20PR) ከአገልግሎት ዘመኑ ጋር ምን ግንኙነት አለው?"
ሳይንሳዊ ምላሽ፦ "የንብርብር ብዛት (Ply Rating) መጨመር የጎማውን አካል (Carcass) ጠንካራ ያደርገዋል። ይህ ጥንካሬ ጎማው በከፍተኛ ሙቀትና ጫና ውስጥም እንኳ ቅርጹን እንዳይቀይር ይረዳዋል። ቅርጹን የጠበቀ ጎማ ደግሞ የጥርስ መላላጡ እኩል (Even Wear) እንዲሆን ስለሚያደርግ፣ ጎማው ሳይቆራረጥ ረጅም ዘመን እንዲያገለግል ያደርጋል።
ምርቶቻችንን ከተጠቀሙ ድርጅቶች በጥቂቱ